📢 የምስራቅ አፍሪካ የሪል እስቴት ኮንፈረንስ

  • Home
  • Uncategorized
  • 📢 የምስራቅ አፍሪካ የሪል እስቴት ኮንፈረንስ

የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) ከAfrican Real Estate Society (AFRES) እና ከዶክሳ ኤቨንትስ ጋር በመተባበር የምስራቅ አፍሪካ የሪል እስቴት ማህበር ኮንፈረንስ በሚቀጥለው ሚያዝያ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በደስታ ያሳውቃል።

ይህን ከፍተኛ የምስራቅ አፍሪካ ክልል ደረጃ ኮንፈረንስ የሚያሳተፉት፦
🏗 የሪል እስቴት አልሚዎች
🏛 የመንግስት ተወካዮችና ፖሊሲ አዋቂዎች
🏦 የፋይናንስ ተቋማትና ባለሀብቶች
🎓 ተመራማሪዎችና የዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች
🏦 አማካሪ ተቋማት
🌍 ከክልሉና ከመላው አፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ባለሙያዎች ለዘርፉ ችግር እና ማነቆ የሆኑትን ነገሮች ለይተውና ነቅሰው በማውጣት በጥናትና ምርምሮቻቸው የመፍትሄ ሀሳብ እንደሚያፈልቁበት ይጠበቃል፡፡

የኮንፈረንሱ ዋና ዋና ዓላማዎች፦

  • ዘላቂ የሪል እስቴት ልማትን ማበረታታት
  • ጥራት ያለው አስተዳደርና ሙያዊ መመሪያዎችን ማጠናከር
  • የምስራቅ አፍሪካ ክልላዊ የዕውቀት ልውውጥን ማበረታታት
  • የግልና የመንግስት ተቋማት የመደጋገፍ ባህልን ማበረታታት
  • ዲጂታል ስርዓቶችን በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ ማስፋፋት

የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር እንደ አስተናጋጅ ተቋም ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ ብሎም በመላው አፍሪካ ውስጥ የሪል እስቴት ውይይት፣ የፖሊሲ ማሻሻያና ፈጠራ ማዕከል እንድትሆን በቁርጠኝነት እየሰራ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *